Building
መስኖ
በግንባታ ላይ ያለ የጀራም መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥር ስራ
Previous
Next

ላሊበላ ጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች

በኢትዮጵያ የቴክኖሎጅና የስልጣኔ ታሪክ ዉስጥ ልዩ ቦታ በሚሰጠዉና ሁሌም የትዉልዶች ኩራት በሆነው የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያን ድንቅ የዲዛይንን ጥበብ በሚያንጸባርቀው ቀደምት የአለም የቴክኖሎጂ ፈርጥ በሆነዉ ላሊበላ ቤተ-ክርስቲያን ልዩ የታሪክ የጥበብ ቅርስ የረጅም ጊዜ ራዕይ አንግቦና ስያሜዉን አግኝቶ በጋፋት ኢንዶውመንት እና በመቅደላ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ የአክሲዮን ሸር እ.ኤ.አ በ2016 የተቋቋመ የልማት ድርጅት ነዉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2030 በምህንድስና፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፍ ጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደረጃ በጥራት እና በብቃት ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ ለመሆን የረጅም ራዕይ በመያዝ በመጠጥ ውሃ፣ በመስኖ፣ በህንጻ፣ በመንገድ፣ በሃይድሮጅኦሎጅ፣ በፕሮጀክትና አካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የጥናት፣ ዲዛይን እና የግንባታ ቁጥጥር ስራዎችን በመስራት ተሳትፎውን በማሳደግ ውጤታማና በስነ-ምግባር እንዲሁም በክህሎት የተካነ አመራርና ሰራተኛ ሃይል በማቀናጀት ለጋራ ራዕይ እንዲሰለፍ በሚያስችል አግባብ እንዲደራጅ በማድረግ ተቋሙ በጥራትና በብቃት የማማከር አገልገሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

 

ራዕይ

እ.ኤ.አ በ2030 በምህንድስና፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፍ በጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ደረጃ በጥራት እና በብቃት ተወዳዳሪና ተመራጭ ኩባንያ ተፈጥሮ ማየት!!

ተልዕኮ

በምህንድስናው ዘርፍ ተወዳዳሪና አዋጭ በሆነ አግባብ በመጠጥ ውሃ፣ መስኖ፣ ህንጻ፣ መንገድና ድልድይ ዘርፍ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር እንዲሁም የፕሮጀክትና አካባቢ ተጽዕኖ ግምገማና ጥናት ስራዎችን በጥራት በማቅረብ በክልሉ ውስጥ የዘርፉን ጥናትና ምርምር በመደገፍ የበኩሉን ሚና መወጣት ነው፡፡

ዕሴቶች

  • የደንበኛ አክብሮት
  • አሳታፊነት
  • የደንበኛ እርካታ
  • ታማኝነት
  • ሚስጥር ጠባቂነት
  • ግልፀኝነት
  • ተጠያቂነት

ኩባንያው አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች

  • በውሃ ስራዎች የጥናት፣ ዲዛይንና ሱፐርቪዥን አገልግሎት፣
  • በህንፃ፣ መንገድና ድልድይ ስራዎች የጥናት፣ ዲዛይንና ሱፐርቪዥን አገልግሎት፣
  • በንግድና ኢንቨስትመንት የማማከር አገልግሎት፣
  • የአካባቢ ኦዲትና ተፅዕኖ ግምገማ /EIA/ እና የጥናት አገልግሎት